1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

"ለሶማሌላንድ ዕውቅና መስጠት የስምምነቱ አካል ነው"

ዓርብ፣ ጥር 17 2016

እአምባሳደር አብዱላሂ ሶማሊያን የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የቀጣናው አለመረጋጋት ምንጭ አድርገው ከሰዋል።«በአንጻሩ ሶማሊላንድ ለቀጣናው መረጋጋት ጉልህ ድርሻ አላት። "ኢትዮጵያም፣ ድንበሯም እንዲከበር እንጠብቃለን። ሁለተኛ ፣ ሶማሊላንድ በሕግ የፀና እውቅና ያለው ግዛት ሆኖ መታወቅ አለበት። ሶማሊላንድ አልሸባብን እና ሽብርተኝነት ትዋጋለች"ብለዋል።

https://p.dw.com/p/4bj2D
የኢትዮጵያ እና የሶማሌላንድ የመግባብያ ስምምነት
የኢትዮጵያ እና የሶማሌላንድ የመግባብያ ስምምነት ምስል TIKSA NEGERI/REUTERS

"ለሶማሌላንድ ዕውቅና መስጠት የስምምነቱ አካል ነው" በኢትዮጵያ የሶማሌላንድ ተወካይ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የተፈራረሙትን የመግባቢያ ስምምነት ለማጠናቀቅ "አሁን ከሁለቱም ወገኖች የቴክኒክ ኮሚቴ በመዋቀር ላይ ነው" ሲሉ በኢትዮጵያ የሶማሊላንድ ተወካይ አምባሳደር አብዱላሂ ሞሀመድ ለዶቼ ቬለ ተናገሩ።"ጉዳዩን ለማጠናቀቅ አሁን ከሁለቱም ወገኖች የቴክኒክ ኮሚቴ በማዋቀር ላይ ነን። እና ይህ ቀድሞውኑ በሂደት ላይ እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ።

(ፊርማውን ትከትሎ) ግንኙነቶች ነበሩ። በሁለቱ ሀገሮች መካከል ጉብኝቶች ነበሩ። ኢትዮጵያ፣የባሕር በር የማግኘት ጥረቷ እና የሀገራት ምላሽየውጭ ጉዳይ እና የአለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትራችን ባለፈው ሳምንት ነው የተመለሱት። እሳቸው እዚህ (አዲስ አበባ) ከእኔ ጋር ነበሩ። ዋና ተግባራቸውም ጉዳዩ መሠረት እንዲይዝ ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር ለመምከር ነበር።
 ይዋል ይደር እንጂ ሁለቱ ኮሚቴዎች ወደ ስራ እንዲገቡ እናደርጋለን። ስለዚህ ይህ በጣም በቅርቡ ይከናወናል ብዬ አስባለሁ።"

የበርበራ ወደብ፤ ሶማሌላንድ
የበርበራ ወደብ፤ ሶማሌላንድ ምስል Brian Inganga/AP/picture alliance

ሶማሊላንድ ለተነሳው ተቃውሞ ምን ትላለች ?

ሶማሊላንድ አለምአቀፍ እውቅና ያገኘ ባይሆንም ባለፉት 30 ዓመታት ራሱ የሚቆጣጠረው ድንበር ፣ የራሱ ሰንደቅ ዓላማ ያለው እና ምርጫ ሲያካሂድ የነበረ ፣ ሕዝቡንም ሲያስተዳድር የቆየ መንግሥት መሆኑን ነው የሶማሊላንድ ተወካዩ የገለፁት።ከሶማሊያ እና ሌሎች ሀገሮች የተነሳውን ተቃውሞ እንዴት እንደሚመለከቱት ጠይቀናቸው ሲመልሱም

"የዓረብ ሊግ፣ ግብፅና ሶማሊያን በተመለከተ፣ በኔ እምነት በዚህ ረገድ ምንም ማድረግ የማይችሉ ይመስለኛል። ያለቀለት የተደመደመ ጉዳይ ነው። አነጋጋሪነቱ የቀጠለው የወደብ ጉዳይከአካባቢው ጋር በተያያዘ ሰፊ ሌላ ዓላማ ላላቸው ግብፆች ምን አስጨነቀን" ብለዋል። በመግባቢያ ስምምነቱ መሠረት ሶማሌላንድ በአፀፋው ምን ታገኝ እንደሆንም ጠይቀናቸው
"ለሶማሌላንድ ዕውቅና መስጠት። ይህ እርግጥ ነው። የዚህ ፕሮግራምም አካል ነው። የስምምነቱም ክፍል እና አካል ነው" በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።

"ሶማሊላንድ አልሸባብን እና ሽብርተኝነት ትዋጋለች" 

አምባሳደር አብዱላሂ ሶማሊያን የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የቀጣናው አለመረጋጋት ምንጭ አድርገው ከሰዋል።ይልቁንም ሶማሊላንድ ለቀጣናው መረጋጋት ጉልህ ድርሻ ያላት መሆኑን ገልፀዋል።

የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቡሂ አብዲ
የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቡሂ አብዲምስል TIKSA NEGERI/REUTERS

"ኢትዮጵያም፣ ድንበሯም እንዲከበር እንጠብቃለን። ሁለተኛ ፣ ሶማሊላንድ በሕግ የፀና እውቅና ያለው ግዛት ሆኖ መታወቅ አለበት። ምክንያቱም እኛ የአካባቢው ጂኦ ፖለቲካዊ መረጋጋት አካል እና ባለድርሻ ነበርን። ባለፉት አመታት አልሸባብን እና ሽብርተኝነትን እየተዋጋን ነበር።" 

«ሶማሊላንድ የሌሎች ሀገሮችም ድጋፍ አላት» 

ሶማሊላንድ በቀጣዩ የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ይህንን ጉዳይ በሚገባ እንደምትይዘውም ለዶቼ ቬለ ቃለ መጠይቅ የሰጡት ተወካይ ተናግረዋል። "ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ወዳጆችም አሉን። ከአምስት የተለያዩ ክልሎች። ለጉዳያችን ብበጣም በጣም አዎንታዊ አመለካከት ያላቸው አባል ሀገራት (የአፍሪካ ሕብረት) አሉን።አወዛጋቢው የኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የመግባቢያ ስምምነት እኛ ሕጋዊ ጉዳይ አለን ፣ የሞራል ጉዳይም አለን ፣ የሚቀረው የፖለቲካ ጉዳይ ብቻ ነው። ለአካባቢው እና ለአህጉሪቱ የምናደርገው በጎ አስተዋፅኦ ተዘንግቷል። የትኛውም አካል የህዝባችን ውሳኔ ላይ ሊወስን አይችልም። ህዝባችን ሕዝበ ውሳኔ አድርጎል። 97.5 በመቶው ነፃ ሀገር መሆንን በመደገፍ ድምጽ ሰጥቷል"።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድምስል Massimo Percossi/Ansa/ZUMA Press/IMAGO

«ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር የመዋጋት ፍላጎት የላትም»

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ትናንት በሰጡት ማብራሪያ ከሶማሊያ ጋር ግጭት ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌለ አብራርተዋል። "ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ህዝብና መንግስት ጋር ለመጣላት፣ ለመዋጋት ፍጹም ፍላጎት የላትም" በዚህ ጉዳይ ላይ በኢትዮጵያ የሶማሊያ ኤምባሲ የሥራ ኃላፊዎችን ለማነጋገር ያደረግሁት ጥረት አልተሳካም።

ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ