1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማርዮ ሞንቲና አዲሱ ካቢኔያቸው

ረቡዕ፣ ኅዳር 6 2004

የ 68 ዓመቱ የምጣኔ ሀብት ምሁር ሞንቲ ከጠቅላይ ሚኒስትርነት በተጨማሪ የገንዘብ ሚኒስትርነቱም ደርበው ይይዛሉ

https://p.dw.com/p/Rwst
ማርዮ ሞንቲምስል dapd

የኢጣልያው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርዮ ሞንቲና የአዲሱ ካቢኔያቸው አባላት ዛሬ ቃለ መሃላ ፈፀሙ ። 16 አባላት ያሉት አዲሱ ኬቢኔ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የጠለቀ እውቀት ያላቸውን ምሁራን ያካተተ ነው ። ከመካከላቸው ሶስቱ ሴቶች ናቸው ። የ 68 ዓመቱ የምጣኔ ሀብት ምሁር ሞንቲ ከጠቅላይ ሚኒስትርነት በተጨማሪ የገንዘብ ሚኒስትርነቱም ደርበው ይይዛሉ ። አዲሱ መንግሥት ኢጣልያን ጨምሮ የዪሮ ተጠቃሚ ሃገራትን ለሚያሰጋው የዕዳ ቀውስ መፍትሄ ያመጣል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል ። የጠቅላይ ሚኒስትር ሞንቲ አዲሱ መንግሥት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተመሰረተ 63 ተኛው የኢጣልያ መንግሥት ነው ።

ሒሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ