1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በስደተኞች የተነሳ ጣሊያን ያላት ስጋት

ማክሰኞ፣ ግንቦት 2 2003

ቀን በቀን ወደ ጣሊያን የሚገቡት የስደተኞች ቁጥር አሁንም አልቀነሰም። ሰሞኑንም ጣሊያን፤ በተለይ ከሰሜን አፍሪቃ አካባቢ ወደ 50000 ስደተኞች ይመጡብኛል ስትል ስጋቷን አሰምታለች።

https://p.dw.com/p/RN1t
ወደ ላይፔዱዛ የሚጓዙ የአፍሪቃ ስደተኞችምስል picture alliance/dpa

ጣሊያን የሌሎች የአውሮፓ አገሮችን እርዳታም እየጠየቀች ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት፤ በምጻሩ NATO ከዚህ ቀደም ከሊቢያ በግጭቱ ምክንያት በርካታ ስደተኞችን አሳፍራ ወደ ላምፔዱዛ ስታመራ አደጋ የደረሰባትን መርከብ ጉዳይ ማጣራት እንደሚጀምር አስታውቋል። ጣሊያን በርካታ ስደተኞች ወደ ግዛቷ ሊመጡ እንደሚችሉ ስጋቷን እያሰማች ነው። ከማግሬብ አገሮች ብቻ ከ 300 ሺህ እስከ 400 ሺህ ሰዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውን የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚንስትቴር ገልጽዋል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ