1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀልባ ስደተኞችና የኢጣልያ ፖሊስ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 6 2003

አንድ ሳምንት በሚጠጋ ጊዜ ውስጥ ቁጥራቸው 250 የሚሆን የጀልባ ስደተኞች በኢጣልያው የሜዲቴራንያን ባህር ክልል ውስጥ ሰጥመዋል ።

https://p.dw.com/p/RI0V
ምስል AP

በትናንትናው ዕለትም ከላምፔዱዛ በሰተሰሜን ምዕራብ በምትገኘው በፓንቴሌሪያ ደሴት አቅራቢያ ሁለት ስደተኞች ጀልባ ውስጥ ሞተው ተገኝተዋል ። ከዚሁ አካባቢ ወደ 250 የሚሆኑ በጀልባ በመጓዝ ላይ የነበሩ ስደተኞች የኢጣልያ ድንበር ጠባቂ መርከብ ደርሰውላቸው ከመስጠም ተርፈዋል ። ስደተኞችን የጫኑ ጀልባዎችን የመፈለጉ ሃላፊነት የኢጣልያ የፊናንስ ፖሊስ አውሮፕላን አብራሪዎች ነው ። ጀልባዎቹ ያሉበትን አቅጣጫ መጠቆም እና የአደጋ ደራሽ ሰራተኞችን ወደ ስፍራው መምራት የአብራሪዎቹ ተግባር ነው ።

ሽቴፋን ትሮንደለ

ሂሩት መለሰ