1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ህብረት አስቸኳይ ስብሰባ

ዓርብ፣ መጋቢት 2 2003

ሊቢያ አሁንም ቀውስ ውስጥ ናት። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በቀጣይ ስለሚወስደው እርምጃ እየተነጋገረ ነው።

https://p.dw.com/p/R8VE
ምስል AP

የአውሮፓ ሀገራት አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጠዋል። ተቃውሞ ፈንድቶባት ወደ አለየለት ብጠብጥ ውስጥ ከገባች አንድ ወር ሊሆናት የቀሩት አራት ቀናት ብቻ ናቸው። የጋዳፊ ሃይሎች አማጺያን በተቆጣጠሩባቸው ቦታዎች ላይ ከምድርና ከሰማይ ቦምቦችን ማዝነባቸውን ቀጥለዋል። ሊቢያ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምን ማድረግ እንዳለበት በመነጋገር ላይ ነው። ፈረንሳይ ከሁሉም ቀድማ ለጋዳፊ ጀርባዋን ሰጥታለች። በቤንጋዚ ኢምባሲ ለመክፈትና ለተቋቋመው ጊዚያዊ የሊቢያ ምክርቤት ድጋፍዋን አሳይታለች። ፖርቹጋል ለጋዳፊ ስልጣንዎ አክትሟል የሚል ደብዳቤ ሰዳለች። የአውሮፓ ሀገራት ዛሬ አስችኳይ ስብሰባ ተቀምጠዋል። የትኩረት አጀንዳቸው ደግሞ ሊቢያ ናት። በመካከለኛው ምስራቅና ሰሜን አፍሪካ መከተል ስላለባቸው ፖሊሲ እና አቋማቸውን በተመለከተ ይነጋገራሉ። ሸዋዬ ለገሠ የብራስልሱን ዛጋቢያችንን ገበያው ንጉሴን ስለስብሰባው በስልክ አነጋግራለች።

ገበያዉ ንጉሤ

መሳይ መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ