1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያዉያን በሊቢያ

ረቡዕ፣ የካቲት 23 2003

የኢትዮጵያ ቅጥረኛ ወታደሮች ወደ ሊቢያ ዘምተዋል የሚለዉን ዘገባም አምባሳደሩ አስተባብለዋል

https://p.dw.com/p/R5H9
የሌላ ሐገር ዜጎች በተገኘዉ መንገድ እየወጡ ነዉምስል dapd

የኢትዮጵያ መንግሥት ሊቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንን ለመርዳት እየጣረ መሆኑን አስታወቀ። የኮሎኔል ሙዓመር ቃዛፊን አገዛዝ በመቃወም በተቀሰቀሰዉ ሕዝባዊ አመፅ ሰበብ ሊቢያ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን መካካል አንዳዶቹ መገደላቸዉ፥ሌሎቹ መደብደባቸዉን፥ ብዙዎች ደግሞ ምግብና መጠለያ ማጣታቸዉን ይናገራሉ።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ እንዳሉት መንግሥታቸዉ ችግረኞቹን ለመርዳት ከሌሎች መንግሥታትና ከርዳታ ድርጅቶች ጋር እየሠራ ነዉ።የኢትዮጵያ ቅጥረኛ ወታደሮች ወደ ሊቢያ ዘምተዋል የሚለዉን ዘገባም አምባሳደሩ አስተባብለዋል።ነጋሽ መሐመድ አምባሳደር ዲናን በስልክ አነጋግሮቸዋል።

ሒሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ