1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ላምፔዱዛ የሚጎርፉ ስደተኞች ና የአውሮፓውያን ስጋት

ማክሰኞ፣ የካቲት 8 2003

ካላፉት 3 ቀናት አንስቶ የኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ በቱኒዝያ ስደተኞች ተጥለቅልቃለች ። እነዚህ ቁጥራቸው ከነዋሪዎቿ በላይ የሆነው በጀልባ ወደ ደሴቲቱ የጎረፉና የሚጎርፉ ስደተኞች ኢጣልያን በእጅጉ አስጨንቀዋል ።

https://p.dw.com/p/R1Em
ምስል picture-alliance/dpa
ሌሎች የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራትና ኢጣልያ እስካሁን ላምፔዱዛ የደረሱትና በመንገድ ላይ ያሉት ብቻ ሳይሆኑ የቱኒዝያውና የግብፁ አመፅ ወደፊት እንደሚዛመትባቸው ከሚያሰጉ ሌሌች የሰሜን አፍሪቃ አገራት ወደ አውሮፓ ሊሸሹ የሚችሉ ስደተኞች ጉዳይም ከወዲሁ ስጋት ውስጥ ከቷቸዋል ። ስደተኞች ከሰሜን አፍሪቃ ወደ ኢጣልያ መጉረፋቸው በኢጣልያ በአጠቃላይም በአውሮፓ ያስከተለው ስጋትና ለመፍትሄውም በመከናወን ላይ ያሉት ተግባራት የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ። ሂሩት መለሰ ተክሌ የኋላ