1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ህብረት የተገን አሰጣጥ መርህ

ሐሙስ፣ መስከረም 20 2003

ደብሊን ሁለት በመባል የሚታወቀው የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የጋራ የስደተኞች አቀባባል መሰረታዊ መመሪያ ተሻሽሎ አባል ሀገራት ተጨማሪ ስደተኞችን እንዲቀበሉ የቀረበውን ሀሳብ በተለይ ጀርመንና ፈረንሳይ አጥብቀው እየተቃወሙ ነው ።

https://p.dw.com/p/PR5s
በግሪክ የኢራን ስደተኛ

በዚህ መርህ የአንድ ተገን ጠያቂ ማመልከቻ ተቀባይነት ማግኘት አለማግኝቱ ስደተኛው መጀመሪያ በረገጠው የህብረቱ አባል ሀገር መወሰኑ ስደተኞች በብዛት በሚጎርፉባቸው አባል ሀገራት አስቸጋሪ አሰራር ሆኗል ። በመላ ጀርመን በሚከበረው የስደተኞች ቀን ፣ የሁለቱ አገራት ተቃውሞና ሌሎችም በአውሮፓ ከስደተኞች አያያዝ ጋር የተገናኙ ጉዳዮች የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች አጥብቀው የሚቃወሟቸው ነጥቦች ናቸው ።

ሪኻርድ ፉክስ

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ