1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከስዑዲ ዐረቢያ ለመመለስ የተዘጋጁ ኢትዮጵያውያን እንግልት፣

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 18 2002

የስዑዲ የአየር ሙቀት መጠን ከ40 ዲግሪ በላይ ሆኖ በቆየባቸው በተለይም ካለፉት ሶስትና አራት ወራት ወዲህ ወደ ትውልድ ሃገራቸው ለመሄድ የመተላለፊያ የይለፍ ወረቀታቸውን በመጠባባቅ ላይ

https://p.dw.com/p/Ov5s
ከስዑዲ ዐረቢያ ለመመለስ የተዘጋጁ ኢትዮጵያውያን እንግልት፣
ምስል AP

ባሉ ኢትዮጽያውያን ላይ ሐሩሩ እጅግ አይሎባቸዋል።

በእስረኛ ብዛት ሳቢያ በሚፈጠረው መተፋፈግም ብዙዎቹ፣ ለከፋ ተላላፊ በሺታ መጋለጣቸውን ታሳሪዎች ይገለጻሉ፡፡ ሴቶቹ ታሣሪዎች፤ መፍትሄ ያገኙ ዘንድ፣ ጠባቂ ፖሊሶችን ሲጠይቁ ፤

ችግራቸው ሊፈታ የሚችለው በሃገራቸው መንግስት በኩል በመሆኑ፤ እነርሱ ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ነው የሚገልጹላቸው።

የሳውዲ ሰብአዊ መብት ማህበር ፣ የጂዳና የመካ አካባቢዎች ሃላፊዎችም ፣ ችግሩን የሳውዲ መንግስት ሳይሆን የስደተኞቹ ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከታቸው የተለያዩ ሃገራት ቆንስሎችና የኤምባሲ መሥሪያ ቤቶች ድክመት፣ ነገሩን ውስብስብ አድርጎታል ሲሉ ይገልጻሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ምንም እንኩዋን በእስር ቤት ያለው ሁኔታ አስክከፊ ነው ቢባልም ፣ ከድልድይ ስር ሆነው እጃቸውን ለፖሊስ ለመስጠት ከተጠለሉበት ድልድይ ፣ የመንግስታቸው እርዳታ ተነፍጎዋቸው በርካታ ችግር ሲያጋጥማቸው የተስተዋሉት ኢትዮጽያውያን ባሳለፍነው ሳምንት መገባደጃ የመጉዋጉዋዣ ሰነድ ከሌላቸው ውጭ፣ ሰነድ ያቀረቡ ኢትዮጽያውያን በአብዛኛው በፖሊስ ተይዘው ማቆያውን እስር ቤት እንደተቀላቀሉ ታውቋል፡፡

ነቢዩ ሲራክ

ሒሩት መለሰ