1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በካምፓላ የተፈጸመው የቦምብ ጥቃት

ሰኞ፣ ሐምሌ 5 2002

በኡጋንዳ መዲና ካምፓላ ትላንት ምሽት በተፈጸሙ ሁለት የቦምብ ከ70 በላይ ሰዎች ሞተዋል። አንደኛው ጥቃት የተፈጸመው በካምፓላ በሚገኝ የኢትዮዽያ ሬስቶራንት ውስጥ ነው።

https://p.dw.com/p/OHSO
ምስል picture-alliance/dpa

ትላንት ምሽት የዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታን ለመመልከት ካምፓላ በሚገኙት የራግቢ ስፖርት ክበብ እና በኢትዮዽያ ሬስቶራንት የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ታድመዋል። ድንገት ግን ከፍተኛ የሆነ ፍንዳታ ተሰማ። በሁለቱም ቦታዎች የፈነዱት ቦምቦች ወዲያውኑ የ64 ሰዎችን ህይወት አጠፋ። በመቶዎች የሚቆጠሩት ክፉኛ ቆሰሉ። ፖሊስ እንዳለው ጥቃቱን የአልሸባብ ቡድን ሳይፈጽመው አይቀርም። በኢትዮዽያ ሬስቶራንት በደረሰው ጥቃት 10 ኢትዮዽያውያንና ኤርትራውያን ህይወታቸውን አጥተዋል።

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ