1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሊቢያ እና የተመድ የስደተኞች መርጃ መስሪያ ቤት

ሐሙስ፣ ሰኔ 3 2002

የመንግስታቱ የስደተኞች ጉዳይ ተመልካች መስሪያ ቤት ሊቢያን ለቆ እንዲወጣ የተጠየቀ መሆኑን ትናንት ይፋ አደረገ።

https://p.dw.com/p/Nmla
ምስል DW-Montage

የሊቢያ ባለስልጣናት የመንግስታቱ ድርጅት ጽ/ቤት የሚያደርገዉን እንቅስቃሴ አቁሞ አገሪቱን ለቆ ይወጣ ዘንድ ያስታወቁ ባለፈዉ ሳምንት ቢሆንም ትዕዛዙ በይፋ የሆነው ባለፈው ማክሰኞ መሆኑን መንበሩ በዠኔቭ የሚገኘው ጽህፈት ቤት ገልጿል። ጽህፈት ቤቱ እንዲወጣ የተወሰነበት ምክንያት እንዳልተገለጸለት አመልክቶዋል። ሊቢያ ከሰሃራ በስተደቡብ ያሉ የአፍሪቃ አገራት ስደተኞች ወደ አዉሮጳ የሚሻገሩባት አገር ናት። ዝርዝሩን የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሀመድ