1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢጣሊያና አፍሪቃዉያን ስደተኞች

ማክሰኞ፣ ጥር 4 2002

በአፍሪቃዉያኑ ላይ የሚፈፀመዉን በደልና ድብደባ የካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲግት አስራ-ስድሰተኛን ጨምሮ የተለያዩ ወገኖች አዉግዘዉታል

https://p.dw.com/p/LSpo
ምስል AP

ደቡባዊ ኢጣሊያ በሚኖሩ አፍሪቃዉያን ሥደተኞች ላይ ባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ የተፈፀመዉን ጥቃት የተለያዩ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እያወገዙት ነዉ።ባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ ሮሳርኖ የተባለችዉ ከተማ ነዋሪዎች ለሰላማዊ ሰልፍ በተሰባሰቡ አፍሪቃዉያን ላይ ሲዝምቱ በተነሳዉ ግጭት በርካታ ሰዎች ቆስለዋል።ከግጭቱ በሕዋላ በሺሕ የሚቆጠሩ አፍሪቃዉያን ከአካባቢዉ ሸሽተዋል።በአፍሪቃዉያኑ ላይ የሚፈፀመዉን በደልና ድብደባ የካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲግት አስራ-ስድሰተኛን ጨምሮ የተለያዩ ወገኖች አዉግዘዉታል።የሮሙ ወኪላችን ተኽለ እግዚ ገብረ እግዚ አብሔር ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ተኽለእዝጊ ገብረየሱስ

ነጋሽ መሀመድ

አርያም ተክሌ