1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ መንግሥትና ዉጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን

ማክሰኞ፣ ጥር 4 2002

ከዉጪ ከተመለሱ አንዳዶቹ ግን የመንግሥት ቢሮ ክራሲ አላሰራም አለን በማለት ያማርራሉ።የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ደ ኤታ ዶክተር ተቀዳ አለሙ በበኩላቸዉ ቢሮክራሲዉን ለማስተካከል መስሪያ ቤታቸዉ እንደሚጥር አስታዉቀዋል

https://p.dw.com/p/LSpM
ምስል picture alliance/dpa

የኢትዮጵያ መንግሥትና ከፍተኛ ባለሥልጣናት በዉጪ ሐገር ከሚኖሩና ከዉጪ ከተመለሱ ኢትዮጵያዉያን ጋር ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ እየተወያዩ ነዉ።በዉይይቱ መክፈቻ ላይ የሐገሪቱ ፕሬዝዳት ግርማ ወልደ ጊዮርዮርጊስ ባደረጉት ንግግር በዉጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ያካበቱትን ሐብትና እዉቀት ለሐገር ልማት እንዲያዉሉት ጥሪ አድርገዋል።ፕሬዝዳቱ በዉጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በልማቱ መስክ እንዲሳተፉ መንግሥታቸዉ ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታዉቀዋል።ከዉጪ ከተመለሱ አንዳዶቹ ግን የመንግሥት ቢሮ ክራሲ አላሰራም አለን በማለት ያማርራሉ።የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ደ ኤታ ዶክተር ተቀዳ አለሙ በበኩላቸዉ ቢሮክራሲዉን ለማስተካከል መስሪያ ቤታቸዉ እንደሚጥር አስታዉቀዋል።ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝሩን ልኮልናል።

ታደሰ እንግዳው

ነጋሽ መሀመድ

አርያም ተክሌ