1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወደ ኬንያ ለመመለስ ብዙ ምክንያቶች ነበሩኝ

ሰኞ፣ መስከረም 14 2016

ወደ ኬንያ ለመመለስ ያነሳሳኝ ሌላው ምክንያት በአሜሪካ ለስድስት ዓመታት ያህል ከቆዮሁ ቦኋላ ከቤተሰብ ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዲኖረኝ እፈልግ ነበር። ይህ የአፍሪቃውያን ልዩ ጠባይ ይመስለኛል። ይህ የቤረሰብ ናፍቆት ወደ ኬንያ ተመልሼ ከቤተሰቦቼ ጋር በመኖር እርካታ የማገኝበት ስለሆነ ነው።

https://p.dw.com/p/4WmAP

ወደ ሃገሩ መመለስ ለሚፈልግ  ሰው የምሰጠው ምክር ገንዘብ የመቆጠብ አስፈላጊነት ነው። በጣም አስፈላጊ የሆነው ነገር ገንዘብ ማካበት ነው።  በመሆኑም ተመልሰህ ወደ አገር ቤት ስትመጣ ማድረግ የምትፈልገውን ነገር ሁሉ ማድረግ እንድትችል ቁዘባ የግድ አስፈላጊ ነው ። ንግድ መጀመር ብትፈልግም ገንዘብ ከቆጠብክ ልትጀምር  ትችላለህ ፤ ወይም ያለህን ፍላጎት የሚያረካና የሚያስፈጽም ሥራ መስራት ይቻላል።