1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

የዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ተሳትፎ በፍርድ ቤት ሊታይ ነው

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 26 2016

የዩናይትድስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዶናልድ ትራምፕ በድጋሚ ለፕሬዚዳንትነት ብቁ ስለመሆናቸው ወይንም አለመኾናቸው ይወስናል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። የቀድሞው ፕሬዚዳንት፣በኮሎራዶና ሜይን ግዛቶች አስቀድሞ በሚካኼዱ ምርጫዎች እንዳይሳተፉ መታገዳቸውን ተከትሎ፣ለሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አስገብተዋል።

https://p.dw.com/p/4atdu
USA Prozess gegen Donald Trump in New York City
ምስል Louis Lanzano/UPI Photo/IMAGO

የአሜሪካ ፍርድ ቤቶች እና የዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ተሳትፎ

ትራምፕ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው የመሣተፋቸው ጉዳይ በሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሊታይ ነው

የዩናይትድስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዶናልድ ትራምፕ በድጋሚ ለፕሬዚዳንትነት ብቁ ስለመሆናቸው  ወይንም አለመኾናቸው ይወስናል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት፣በኮሎራዶና ሜይን ግዛቶች አስቀድሞ በሚካኼዱ ምርጫዎች እንዳይሳተፉ መታገዳቸውን ተከትሎ፣ለሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አስገብተዋል።

የዶናልድ ትራምፕ ዕገዳ

ዶናልድ ትራምፕ፣በኹለቱ ግዛቶች አስቀድሞ በሚካኼዱ ምርጫዎች እንዳይሳተፉ እግድ የተጣለባቸው፣ባለፈው ምርጫ ከፕሬዚደንት ጆሴፍ ባይደን ጋር ተወዳድረው የምርጫንውን ውጤት ባለመቀበላቸው  ደጋፊዎቻቸው በቀሰቀሱት ረብሻ ምክንያት ፣ በሀገሪቱ ህገ መንግስት ላይ የተቀመጠውን የአመጽ አንቀጽ በመጥቀስ ነው።

የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዕገዳ በዘንድሮው ምርጫ ላይ የሚሳድረውን ህጋዊና ፖለቲካዊ አንድምታ አስመልክቶ፣በቨርጂኒያ ግዛት በህግ ባለሙያነት የሚያገለግሉት፣ ዶክተር ፍፁም አቻምየለህን አነጋግረናቸዋል።ትራምፕ ለ 20 ደቂቃ እስር ላይ ነበሩ

"ሰሞኑን እየተካሄደ ያለው ነገር፣ በኮሎራዶ ህግ መሠረት  ህገ መንግስታዊ ሐተታ የሚሰጠው ወይም የሚወስነው አንድ ሰው በእጩነት ይሳተፋል ወይም አይሳተፍም የሚለውን የሚወስነው ፍርድ ቤት ነው። የታችኛው የወረዳ ፍርድ ቤት ይሳተፋሉ ብሎ ወሰነ። ተከራካሪዎች ወደ ኮሎራዶ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ወሰዱት።የኮሎራዶ ጠቅላይ ፍርድ  ትራምፕ መሳተፍ አይችሉም ብሎ ወሰነ።ይሄ እንግዲህ በኮሎራዶ  ህግ መሰረት ነው።"

የኮሎራዶ ግዛት ፍርድ ቤት
ዶናልድ ትራምፕ፣በኹለቱ ግዛቶች አስቀድሞ በሚካኼዱ ምርጫዎች እንዳይሳተፉ እግድ የተጣለባቸው፣ባለፈው ምርጫ ከፕሬዚደንት ጆሴፍ ባይደን ጋር ተወዳድረው የምርጫንውን ውጤት ባለመቀበላቸው  ደጋፊዎቻቸው በቀሰቀሱት ረብሻ ምክንያት ፣ በሀገሪቱ ህገ መንግስት ላይ የተቀመጠውን የአመጽ አንቀጽ በመጥቀስ ነው።ምስል David Zalubowski/AP Photo/picture alliance

የሜይን ግዛት የውጪ ግንኙነት መስሪያ ቤት ሀላፊ ቬና ቤሎውስ፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት በግዛቲቱ ውስጥ ፓርቲያቸውን ወክለው በቅድመ ምርጫው እንዳይወዳድሩ ማገዳቸውን በተመለከትም፣ ዶክተር ፍጹም የሚከተለውን ብለዋል።የአሜሪካ ምርጫ ዉጤት በአዉሮጳ ላይ ያለዉ አንደምታ 

"የሜይኑ ግን ለየት ያለ ነው። በሜይን ክፍለ ግዛት ህግ መሠረት ማን መስፈርቱን ያሟላል ወይም አያሟላም የሚለውን በተለምዶ ብቁነትን የሚመለከተው የህገ መንግስቱን አንቀጽ ዐይቶ ያሟላል አያሟላም  የሚለውን የሚወስነው፣ የሜይን ክፍለ ግዛት የምርጫ ጉዳይን የሚያየው የውጭ ግንኙነት መስሪያ ቤት ነው። የቢሮው ሃላፊ ስልጣን አላት።የራሷን ሰዎች ያላቸውን ተቃውሞ እና ድጋፍ ካስሙና ካዳመጡ በኇላ፣ፍርድ ቤት ሳይሆን እሷ ወሰነች፤  ማለት ትራምፕ በሜይን ውስጥ መሳተፍ አይችሉም ምክንያቱም በአመጹ ውስጥ ስለተሳተፈ ወይም የተሳተፉትን ስለረዳ ብላ ወሰነች።

በውጭ ግንኙነት ኃላፊዋ ላይ ትራምፕ ያቀረቡት ክስ

ውሳኔው ያበሳጫቸው ዶናልድ ትራምፕ፣ለዚህ ውሳኔ ይግባኝ በመጠየቅ፣በሜይን ግዛት ውጪ ግንኙነት ኃላፊ ላይ ክስ መስርተዋል።

በኮሎራዶ ግዛት ፍርድ ቤት የተጣለባቸውን ዕገዳም፣ የሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዲሽርላቸው ይግባኝ ጠይቀዋል።

ትራምፕና ደጋፊዎቻቸው፣ እገዳዎቹ  በሙሉ ፖለቲካዊ ተነሳሽነት አላቸው ባይ ናቸው።የአሜሪካ ዴሞክራሲ

ተፎካካሪያቸው የሆኑ ዴሞክራቶች፣ ህገ መንግስታዊ ባልሆነ መንገድ፣የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ከምርጫ በማገድ የአሜሪካ መራጮችን መብት እየገደቡ ናቸው በማለት ይወቅሳሉ።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት የሕግ ቡድን እንደሚለው፣ የዛሬ አራት ዓመት ከተካሄደው ምርጫ በኋላ ጥር ስድስት ላይ የነበረው ግርግር እንደ አመጽ የማይቆጠር ሲሆን፣ ትራምፕ በዚያ ቀን ለደጋፊዎቻቸው  የስጡት ማሳሰቢያ የቅስቀሳ ይዘት አልነበረውም።

ትራምፕ የሰጧቸው መግለጫዎችም፣ በሃገሪቱ ህገ መንግስት የመጀመሪያ ማሻሻያ ጥበቃ እንደሚሰጣቸው አስረድተዋል።

ዋይት ሃውስ ካፒቶል
አሁን እየተጠበቀ ያለው፣አቤቱታ የቀረበለት የዩናይትድስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህገ መንግስታዊ ጉዳዩን ተመልክቶ፣ትራምፕ የሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩነትን ካሸነፉ በአጠቃላዩ ምርጫ መወዳደር ይችሉ እንደሆን የሚሰጠው ብይን ነው።ምስል Leigh Vogel/Getty Images for Resist Trumpism

ተጠባቂው አሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ

አሁን እየተጠበቀ ያለው፣አቤቱታ የቀረበለት የዩናይትድስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህገ መንግስታዊ ጉዳዩን ተመልክቶ፣ትራምፕ የሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩነትን ካሸነፉ በአጠቃላዩ ምርጫ መወዳደር ይችሉ እንደሆን የሚሰጠው ብይን ነው።

የህግ ባለሙያው ዶክተር ፍጹምን ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዉሳኔ ምን እንደሚጠበቅ ጠይቀናቸው፣ እንደሚከተለው መልሰዋል።ዩናይትድ ስቴትስ ዴምክራሲ ወደ ኋላ ከተመለሰባቸው ሃገራት ተርታ

"በአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውስጥ ስድስቱ ዳኞች በሪፐብሊካን ፓርቲ  ስለሆነ የተሾሙት፣ከእዛም ውጭ ያሉት ቢሆኑ ይሄ  አገር በዚህ ምክንያት ሌላ ውጥንቅጥ ውስጥእንዲገባ ስለማይፈልጉ፣ሕዝቡ ራሱ ይወስን ብለው ይወስናሉ ብዬ ስለማስብ፣እኔ እንደሚመስለኝ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ራሱ ትራምፕ ብቁ አይደሉም የሚል አይመስለኝም።"

የሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ከዓመታት በፊት ለፕራዚዳንታዊ ምርጫ በቀረቡትና ውጤታቸው አወዛጋቢ በነበረው የጆርጅ ቡሽና አልጎርን ጉዳይ ከተመለከተ በኇላ፣ በከፍተኛ ደረጃ  የሚያየው ጉዳይ በመሆኑ ብዙዎች በጉጉት የሚጠብቁት ሆኗል።

ታሪኩ ኃይሉ

ታምራት ዲንሳ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር