1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: በፈተና ውስጥ የምትገኘው ታዳጊ

ረቡዕ፣ መጋቢት 4 2016

የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ታዳጊ እፁብድንቅ አስቻለው ከአሥር ዓመት በፊት የጀመራት የህመም ሥሜት አድጎ አሁን ላይ ለእግር እና ለጀርባ ጉዳት እንደዳረጋት ትናገራለች ፡፡በእርግጥ ታዳጊዋ ባጋጠማት ጉዳት የተነሳ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ብትገኝም ከመማር አላገዳትም፡፡

https://p.dw.com/p/4dT0g

በዕለት ተዕለ ህይወቷ የአናቷና የታናሽ ወንድሟ ቤተሰባዊ ድጋፍ እንደማይለያትና በትምህርት ቤት ያሉ ሰዎችም በጎ አስተያየት እንደሚሰጧት ጠቅሳለች ፡፡
ታዳጊዋ አሁን ላይ የ12 ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለመውሰድ በዝግጅት ላይ እንደምትገኝ ትናገራለች ፡፡ የሥዕል ጥበብ ዝንባሌ እንዳላትና በተወሰነ ደረጃም እሞክራለሁ የምትለው የ18 ዓመት ታዳጊ  ወደፊት ዲዛይነር የመሆን ህልም እንዳላት ገልጻለች ፡፡ እንደእሷ ለጉዳት የተጋለጡ ወጣቶች ባሉበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ማሰብና የቻሉትን ያህል መጣር እንደሚገባቸውም ጠቅሳለች ፡፡
የእፁብድንቅ አስቻለው ወላጅ እናት ወይዘሮ እርቅነሽ ቀጸላ እፁብደንቅን ከታናሽ ወንደሟ ጋር በመሆን ወደ ትምህር ቤት በመውሰድና በማምጣት እንደሚደግፏት ይናገራሉ ፡፡ ያም ሆኖ ብዙ አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንዳሉት ነው ወይዘሮ እርቅነሽ የገለጹት ፡፡
የልጃቸው ጉዳት በህክምና ሊድን የሚችል ሥለመሆኑ በሀኪም ማስረጃ ቢረጋገጥም ባላቸው አነስተኛ ገቢ የተነሳ ለማሳካም አለመቻላቸውን የጠቀሱት ወይዘሮ እርቅነሽ “ ልጄ እንድትድን እፈልጋለሁ ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ባለው አቅም እንዲደግፈኝ እማጸናለሁ “ ብለዋል ፡፡ #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘገባ: ሊሻን ዳኜ
ቪድዮ: ሸዋንግዛው ወጋየሁ