1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ዲጂታል ዓለምኢትዮጵያ

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የፎቶ ጥበበኛዋ ወጣት

ማክሰኞ፣ መጋቢት 3 2016

በሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ ላይ የፎቶግራፍ አገልግሎት ከሚሰጡት በርካታ ወጣቶች መካከል ማርታ መንጆ በጣት ከሚቆጠሩ ሴት የፎቶ ባለሙያዎች አንዷ ናት ፡፡ ማርታ ወደ ፎቶግራፍ ሙያ እንዳዘነብል ምክንያት የሆነኝ ወንድሜ ነው ትላለች ፡፡

https://p.dw.com/p/4dQHV

“ወንደሜን ፎቶ ቤት አግዘው ነበር “ የምትለው ማርታ “ ፍላጎቱ ስለነበረኝ በዛው የፎቶ አነሳስ ጥበብን እንድቀስም ዕድል ፈጥሮልኛል ፡፡ በተጨማሪም አጭር የፎቶግራፍ ሥልጠና በመውሰድ እና ካሜራ በመግዛት ወደ ሙያው ልገባ ችያለሁ “ ብላለች ፡፡
ቤተሰቦቿ በትምህርት እንድትቀጥል ይፈልጉ እንደነበር የምትናገረው ማርታ “ አኔ ግን አሁን በዚሁ ሙያ ተሰማርቼ እገኛለሁ ፡፡ ጥሩ የገቢ ምንጭም እያገኘሁበት ነው ፡፡ ሰዎች እኔን ሲያዩ ደስ ይላቸዋል ፡፡ ብዙዎችም ያበረታቱኛል ፡፡ በተለይም በሀይቁ ዳርቻ ላይ በጀልባ ለመዝናናት የሚመጡ ሰዎች ፎቶ እንዳነሳቸው ስጠይቃቸው ፍቃደኛ ናቸው  “ ብላለች፡፡ 
በቀጣይ በፎቶግራፍ ሙያ የተሻለ ቦታ መድረስ እንደምትፈልግ የጠቀሰችው ማርታ “ ባለብኝ የገንዘብ እጥረት ምክንያት ለጊዜው ተግባራዊ ማድረግ ባለችልም ወደፊት ግን የራሴን የፎቶግራፍ ስቱዲዮ ለመገንባት ሀሳቡ አለኝ፡፡ ይህን ለማሳካት ጥረት እያደረኩ እገኛለሁ “ ብላለች፡፡
#ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘገባ: ሊሻን ዳኜ
ቪድዮ: ሸዋንግዛው ወጋየሁ