1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወደ ሔይቲ ሰላም አስከባሪ በምትልከው ኬንያ ጥያቄ ተነስቷል

ሐሙስ፣ መስከረም 24 2016

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት ባለፈው ሰኞ በኬንያ የሚመራ ዓለማቀፍ የፖሊስ ኃይል የወሮበሎች መፈንጫ ወደሆነችው ሔይቲ እንዲገባና ሰላም እንዲያስከብር ወሳኔ አሳልፏል ። ሔይቲ በአሁኑ ወቅት መንግስታዊ መዋቅሮቿ ፈርሰው ወረበሎችና የወንጀለኛ ቡድኖች የተቆጣጠሯት የሁከት ምድር በመሆን የምትታወቅ ሁናለች።

https://p.dw.com/p/4XAOo
የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ታጣቂዎች በሔይቲ ጎዳናዎች
የቀድሞ ፖሊስ አባላት በሔይቲ ጎዳናዎች ተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ አደባባይ የወጡት እንዲህ እንደታጠቁ ነው ፦ ፎቶ ከማኅደርምስል Ralph Tedy Erol/REUTERS

በሀገሪቱ ፖለቲከኞች ዘንድ ከወዲሁ ጥያቄ አጭሯል

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት ባለፈው ሰኞ በኬንያ የሚመራ ዓለማቀፍ የፖሊስ ኃይል የወሮበሎች መፈንጫ ወደሆነችው ሔይቲ እንዲገባና ሰላም እንዲያስከብር ወሳኔ አሳልፏል ። ከላቲን አሜሪካና ካሪቢያን አገሮች በ19ኛው ክፍለ ዘመን የቅኝ አገዛዝን አስወግዳ የጥቁር ሕዝቦች ሪፑብሊክ በመሆን በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሿ ሔይቲ በአሁኑ ወቅት መንግስታዊ መዋቅሮቿ ፈርሰው ወረበሎችና የወንጀለኛ ቡድኖች የተቆጣጠሯት የሁከት ምድር  በመሆን ሁናለች። የሰላም ማስከበሩን በግንባር ቀደምነት የምትመራው ኬንያ ላቲን አሜሪካ ድረስ ተጉዛ ምን ይጠብቃታል? በሀገሪቱ ፖለቲከኞች ዘንድ ከወዲሁ ጥያቄ አጭሯል ።

የመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት ባለፈው ሰኞ በኬንያ የሚመራ ዓለማቀፍ የፖሊስ ኃይል ወደ ሀይቲ እንዲገባና አገሪቱን እያመሱ ካሉት የከተማ ወረበሎችና የጦር አበጋዞች በመታደግ ሰላም እንዲያስከብር የሚፈቅድ ውሳኔ አስተላልፏል።

ሀይቲ ከላቲን አሜሪካና ካሪቢያን አገሮች የመጀምሪያዋ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የቅኝ አገዛዝን ያሰወገደች በአካባቢው ቀዳሚያዋ የጥቁር ሕዝቦች ሪፑብሊክ በመሆን የምትጥቀስ ቢሆንም፤ በአሁኑ ወቅት ግን መንግስታዊ መዋቅሮቿ ፈርሰው ወረበሎችና የወንጀለኛ ቡድኖች የተቆጣጠሯት የሁከት ምድር  በመሆን የምትታወቅ ሁናለች። አገሪቱን መምራትና ማስተዳደር ያቃታቸውና በነፍሰገዳዮች የተገደሉትን ፕሬዝዳንት ጆቪኔል ሞይሴን ተክተው በተጠባባቂ ፕሬዝደንትነት የተሰየሙት ሚስተር አሪየል ሄንርይና የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ ሚስተር አንቶኒዮ ጉቴሬሽ፤ ዓለማቀፍ የፖሊስ ኃይል ወደ ሀይቲ ገብቶ ሕግና ሰላም እንዲያስከብር በተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተክትሎ ነበር፤ ባለፈው ሰኞ የፀጥታው ምክርቤት ይህን ውሳኔ ያስተላለፈው።

ሔይቲ ወረበሎችና የወንጀለኛ ቡድኖች የተቆጣጠሯት የሁከት ምድር  በመሆን የምትታወቅ ሁናለች።
ሔይቲ በአሁኑ ወቅት መንግስታዊ መዋቅሮቿ ፈርሰው ወረበሎችና የወንጀለኛ ቡድኖች የተቆጣጠሯት የሁከት ምድር  በመሆን የምትታወቅ ሁናለች። ምስል Odelyn Joseph/AP Photo/picture alliance

በሀይቲ ከዚህ ቀደምም የውጭ ኃይሎች በልዩ ልዩ ሰበቦችና በሰላም አስከባሪ ስም ገብተው የነበር ቢሆንም፤ ባብዛኝው  ግን ውጤታማ እንዳልነበሩ ነው የሚጠቀሰው። እ እ ከ2004 እስከ 2017 በአገሪቱ የነበረው የመንግስታቱ ድርጅት የሰላም ስከባሪ ኃይል ከተላከበት ተልኮ ውጭ በሙስና ተዘፍቆ፤ በጾታዊ ጥቃት ተክሶ በታቃውሞ እንዲወጣ መደረጉን የሚጠቅሱ ታዛቢዎች በአሁኑ ወቅት የሚላከው ኃይል የተሻለ መሆኑን  ይጠራጠራሉ።

ይሁን እንጂ ይህ የአሁኑ ኃይል የተለየ እንደሆነና ግቡም ውስን እንደሆነ ነው በፀጥታው ምክርቤት የዩናይትድ ስቴትስ ተወካይ  ወይዘሮ ሊንዳ ግሪን ፊልድ የሚናገሩት፤ "ህብረብሄራዊ ኃይል ወደ ሀይቲ ገብቶ ሀየቲዎች ከወረበሎች ጋር የሚያደርጉትን ትግል እንዲያግዝ ጥያቄ የቀረበው ከሀይቲ መንግስትና ከመንግስትቱ ድርጅት ዋን ጸሐፊ ነው። አሚሪካ የሀሳቡን በመደግፍ ለተልኮው ማስፈጸሚይ ካንድ መቶ ሚዮን ዶላር በላይ ለግሳለች” በማለት ኬንያ ኃላፊነቱን ለመውሰድ ፈቃደኛ በመሆኗ አመስግነዋል።

ኬንያለሀይቲ ሰላም አስከብሪ ኃይል አንድ ሺ ፖሊሶችን እንደምታሰማራና  ግንባር ቀደም ተሰላፊ እንደምትሆን ስትገልጽ የቆየች ሲሆን፤ የፀጥታው ምክር ቤትን ውሳኔ አገራቸው በደስታ የምትቀበል መሆኑን ፕሬዝዳንቷ ዊሊያም ሩቶ አስታውቀዋል። " ለኛ ለኬንያውያን ይህ ውሳኔ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ነው። የቅኝ ገዥዎችን አስከፊ አገዛዝ የምናውቅና ለነጻነት ትግልም ትልቅ ዋጋ የከፈልን ህዝቦች ነን” በማለት ባሁኑ ወቅትም ከሀይቲ ጎን የመቆም ሞራላዊ ግዴታ ያለባቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

ፕሬዝዳንት ሩቶ አገራቸው  በሰላም አስከባሪ ተልኮ በመሳተፍ ከምስራቅ ቲሞር እስከ የቀድሞው ዩጎዝላቪያና በዓፍርሪካም በዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎና ሶማሊያ ልምድ ያላት መሆኑን በመግለጽ  ሁልግዜም ለስላምና ደህንነት መረጋገጥ ዘብ  እንደሚቆሙና ዛሬም ለሀይቲ ጀርባቸውን እንደማይሰጡ ገልጸዋል።

ሔይቲ የወሮበሎች መፈንጫ ሁናለች
ከላቲን አሜሪካና ካሪቢያን አገሮች በ19ኛው ክፍለ ዘመን የቅኝ አገዛዝን አስወግዳ የጥቁር ሕዝቦች ሪፑብሊክ በመሆን በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሿ ሔይቲ የወሮበሎች መፈንጫ ሁናለች ።ምስል Richard Pierrin/AFP

ይህ ዓለማቀፍ ኃይል ከሌሎች ከዚህ ቀደም በተባበሩት መንግስታት ስር ከተሰማሩ የሰላም አስከባሪ ኃይሎች የተለየ እንደሆነና የሚመራውም በመንግስታቱ ድርጅት ሳይሆን በኬንያ እንደሚሆን ተደጋግሞ ተገልጿል። ከጃማይካ ባህማስና ሌሎች የካሪቢያን አገሮችም ተጨማሪ የፖሊስ ሀይል የሚላክ ቢሆንም  ዋናው የተልኮው ባለቤት ግን ኪንያ ናት ተብሏል።

ኬንያይህን በማድረጓ ለወታደሮቿ የበለጠ ስልጠናና ልምድ፣ የመሳያሪና የገንዘብ ድጋፍ፤ ክሁሉም በላይ፤ በዓለማቀፉ ፖለቲካ ክፍተኛ ቦታ የሚያስገኝላት እንደሚሆን እየተነገረ ነው። ይሁን እንጂ የሀይቲ ወረበሎችና ታጣቂዎች የሚዋጉት በሚያውቁት አካካባቢ በመሆኑና የተደራጁም በመሆናቸው፤ በተጨምሪም የቋንቋና ባህል ልዩነትም ያለ በመሆኑ ተልኮው በቀላሉ የሚሳካ ስለመሆኑ ጥያቄ የሚይነሱት ጥቂቶች አይደሉም። የቀድሞው የኬንያ የመከላከያ ሚኒስተር ኡጉዌና ዋማልዋ ይህንኑ ጥያቄ ከሚያነሱት አንዱ ናቸው። " በመጀመሪያ ደረጃ ወደ ሀይቲ በመሄድ የምናገኘው ጥቅም ምንድን ነው?  12ሺ  ኪሎሜትር እርቀት ላይ በምተገኘውና ብዝዎቹ ወታደሮቻችን ቁንቋቸውን በማይረዱባት አገርስ መግባቱ አስፈላጊ ነው ወይ?” በማለት የአገራቸው መንግስት ከጅምሩ የወሰደውን ተነሳሽነት ተችተዋል።

ፕሬዝዳንት ሩቶና መንግስትቸው ግን  በጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔ መሰረት ሀላፊነነታቸውን ለመወጣት ወታደሮቻቸውን የቋንቁና ሌሎች ተጨማሪ ስልጠናዎችን እንዲወስዱ እያደረጐ እንደሆነ እይተገለጸ ሲሆን፤ የስላም አሰከባሪ ኃይሉም በታህሳሥ መጨረሽ ወይም የጥር ወር መጀመሪያ ላይ ወደ ሀይቲ ይላካል ተብሎ ይጠበቃል

ገበያው ንጉሤ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሠ