1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አስደማሚ ርብርብ በምሽት የባሕር ላይ ስደተኞችን ለማዳን

ረቡዕ፣ መጋቢት 11 2016

እጅግ አስደማሚ በሆነ የምሽት ሕይወት አድን ርብርብ 75 የባሕር ላይ ስደተኞች ሰጥመው ከመሞት ተርፈዋል ። ሰሜናዊ የአፍሪቃ አቅጣ በዓለም አቀፍ የባሕር ወሰን የሜዲቴራኒያ ባሕር ላይ ስደተኞቹን ከመስጠም የታደጉት አትራፊ ያልሆነ የመርከብ ተቋም ሕይወት አድን ሠራተኞች ናቸው

https://p.dw.com/p/4dwmy

እጅግ አስደማሚ በሆነ የምሽት ሕይወት አድን ርብርብ 75 የባሕር ላይ ስደተኞች ሰጥመው ከመሞት ተርፈዋል ። ሰሜናዊ የአፍሪቃ አቅጣ በዓለም አቀፍ የባሕር ወሰን የሜዲቴራኒያ ባሕር ላይ ስደተኞቹን ከመስጠም የታደጉት አትራፊ ያልሆነ የመርከብ ተቋም ሕይወት አድን ሠራተኞች ናቸው ። የስደተኞቹ ጀልባ ስትገለበጥ 45 ሰዎች ውኃ ውስጥ ቢገቡም የሕይወት አድን አልባሳትን በማደል ከመስጠም ታድገዋቸዋል ። እሁድ ምሽት በተደረገው የሕይወት አድን ርብርብ እንደ ዕድል የሰጠመ የለም ። ሆኖም እንደ ዓለም አቀፍ ተቋማት መረጃ ባለፈው የጎርጎሪዮስ ዓመት ብቻ 2,500 ስደተኞች ሰጥመዋል ወይ ተሰውረዋል ። ባለፉት ሰባት ወራት ደግሞ 226 ሰዎች የደረሱበት ዐይታወቅም ።

የቪዲዮ ዘገባ፦ ዶይቸ ቬለ
ምንጭ አሶሺየትድ ፕሬስ