1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትግራይ አማራ የሰላም መድረክ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 4 2011

የትግራይና አማራ ክልሎች የሰላም መድረክ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ዛሬ ተካሄደ፡፡ በመድረኩ የሁለቱን ህዝቦች ዘመናት የተሻገረ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠነክሩ፣ ስጋት ለፈጠሩ ክስተቶች መፍትሔ የተባሉ ሃሳቦች ቀርበውበታል፡፡

https://p.dw.com/p/3A3Su
Einweihung Mekele Industriepark Äthiopien
ምስል DW/Yohannes G/Egziabhare

በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን ጨምሮ የተሻለ ምክረ ሀሳብ ለፖለቲካ መሪዎች ለማቅረብ በቀጣይነት እንደሚሰራም ተጠቁሟል፡፡ የመድረኩ አስተባባሪና ጥናት አቅራቢ ዶክተር ገብረየሱስ ተክሉ የግጭት ስጋቶች ለማምከን ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና መገናኛ ብዙሃን ገንቢ ሚና መጫወት አለባቸው ብለዋል፡ ፡በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች የሚስተዋሉ ግጭቶችና የግጭት ስጋቶች ለመከላከል ሁሉም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡ የመቀሌው ዘጋቢያችን ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

 

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ

 

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ