1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእርዳታ ጥሪ

ሰኞ፣ ጥር 25 2012

አንድ አስተያየት ሰጭ በአሁኑ ሰዓት በቤተክርስትኑ ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ተጠልለው እንደሚገኙ እና እስከ ትናንት ያያቸው የመንግስት አካል የለም ብለዋል ፡፡የሀረሪ ክልል የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ናስር ዩያ በሰጡት ምላሽ ከቤት ንብረት የተፈናቀሉት ዜጎች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ የማድረግ ስራ ተሰርቷል ብለዋል ፡፡

https://p.dw.com/p/3XDUO
Karte Äthiopien englisch

የእርዳታ ጥሪ

በሀረር በቅርቡ የጥምቀት በዓል ዋዜማ እና በበዓሉ ዕለት የተከሰተውን ግጭትና ብጥብጥ ተከትሎ ከሁለት መቶ በላይ አባወራዎች ከቤት ነብረት ተፈናቅለዋል ፡፡ እነዚህ በቤተክርስትያን ተጠልለው የሚገኙ ዜጎች መንግስት እስካሁን ምንም አይነት ድጋፍ አላደረገልንም ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል ፡፡በሀረር ገብረኤል ቤተክርስትያን ተጠልለው ከሚገኙት እነዚህ ነዋሪዎች መካካል ለDW አስተያየት የሰጡ እናት የተፈጠረውን ግጭት እና ብጥብጥ ተከትሎ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በቤተክርስትያን ከተጠለሉ አስራ ስድስት ቀናት መቆጠሩን ተናግረዋል  ፡፡አስተያየት ሰጪዋ እንዳሉት ከዚያን ግዜ አንስቶ በቤተክርስትያኒቱ ተጠልለው እንዳሉ እና የአካባቢው ህብረተሰብ እና አማኙ ካደረገላቸው ድጋፍ ባለፈ እስካሁን መንግስት ምንም ዓይነት ድጋፍ አላደረገልንም ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል፡፡አንድ ለቤተክርስትያኒቱ ቅርበት ያላቸው አስተያየት ሰጭ በበኩላቸው በአሁኑ ሰዓት በቤተክርስትኑ ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ተጠልለው እንደሚገኙ እና እስከ ትናንት ያያቸው የመንግስት አካል የለም ብለዋል ፡፡የሀረሪ ክልል የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ናስር ዩያ የተፈጠረውን ሁኔታ በተመለከተ በሰጡት ምላሽ በመንግስት መዋቅር ስጋትን ለመቅረፍና ከቤት ንብረት የተፈናቀሉት ዜጎች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ የማድረግ ስራ ተሰርቷል ብለዋል ፡፡ ኃላፊው በቀጣይም ስጋትን ለማስወገድ ህብረተሰቡን የማወያየት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ ከጥምቀት በዓል ዋዜማ አንስቶ በከተማይቱ በርካታ ጉዳት በሰው እና በንብረት ላይ ያደረሰውን ድርጊት ተከትሎ ሰማንያ ሰባት ያህል ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ፖሊስ መግለፁ ይታወሳል ፡፡
መሳይ ተክሉ
ታምራት ዲንሳ
አዜብ ታደሠ