1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሀረሩ የፍንዳታ ጥቃት ተጠርጣሪዎች ታሰሩ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 20 2014

ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ አራት ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ እየተካሄደ እንደሚገኝ ፖሊስ ጠቁሟል። ኮምሽነር ነስሪ በጉዳዩ ላይ ያልተረጋገጠ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ እያሰራጩ ይገኛሉ ያሏቸው አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

https://p.dw.com/p/4AZP2
Äthiopien - Harar
ምስል Mesay Tejkelu/DW

በሀረሩ የፍንዳታ ጥቃት ተጠርጣሪዎች ታሰሩ

ከቀናት በፊት በሀረር ከተማ አንድ ሆቴል ውስጥ በመዝናናት ላይ ባሉ ሰዎች መካከል በተጣለ «ቦምብ መሰል» ነገር በመዝናናት ላይ የነበሩ ስምንት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን እና ተጎጅዎች ወደ ህክምና ተቋም መወሰዳቸውን የክልሉ ፖሊስ አስታውቋል። ከተጎጅዎች አራቱ ህክምና አግኝተው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ የተቀሩት ህክምና ላይ መሆናቸውን እና እንደሚገኝ ገልፃል። በወንጀሉ አራት ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያካሄደም ይገኛል።  ፖሊስ ያልተረጋገጠ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ እያሰራጩ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል አሳስቧል።

የሀረሪ ፖሊስ ኮምሽን ኮምሽነር ነስሪ ዘከርያ ለሚዲያ በሰጡት መረጃ በከተማው አንድ ሆቴል በመዝናናት ላይ በነበሩ ሰዎች መካከል ቦምብ መሰል ነገር ተወርውሮ ስምንት ሰዎች መጎዳታቸውን ተናግረዋል። ኮምሽነሩ ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ አራት ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ እየተካሄደ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ኮምሽነር ነስሪ በጉዳዩ ላይ ያልተረጋገጠ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ እያሰራጩ ይገኛሉ ያሏቸው  አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

በሀገሪቱ " ከኢድ እስከ ኢድ " በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ባለው ዝግጅት በሀረር የኢድ አልፈጥር እና ሸዋል ኢድ በዓልን በደመቀና ሰላማዊ በሆነ  መልኩ እንዲከበር የተለያዩ የፀጥታ አካላት በጋራ እየሰሩ ነው ተብሏል። መሰል ችግሮችን በመከላከል በኩል ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር እንዲተባበርም ጠይቀዋል።

የክልሉ ፀጥታ ምክርቤት ትናንት ባወጣው መግለጫ ድርጊቱን የፈፀሙ አካላት በአፋጣኝ ተጠያቂ በማድረግ ህግ የማስከበር ስራ ተጠናክሮ እንደሚሰራ ገልፃል።

መሳይ ተክሉ
ልደት አበበ
አዜብ ታደሰ